የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ብጥብጥ በቀሰቀሰው የግብር ጭማሪ ህግ ላይ እንደማይፈርሙ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ብጥብጥ በቀሰቀሰው የግብር ጭማሪ ህግ ላይ እንደማይፈርሙ ተናገሩ ማክሰኞ በተፈጠረው አለመረጋጋት ለተገደሉት እና ለተጎዱ ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል። በህጉ ማሻሻያዎች ላይ ከሀገሪቱ የወጣት ተወካዮች ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ሁሉም ፓርቲዎች እና የፖለቲካ ሃይሎች በማሻሻያው ላይ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል። ሩቶ በሀገሪቱ እድገት ዙርያ ፍላጎት ያላቸው ሁሉ ሕግ የማውጣት ሂደቱ ላይ የሕግ የበላይነት እና የኬንያን ሕገ-መንግስታዊ ስርዓት በማክበር እንዲሳተፉ ጠይቀዋል። በማክሰኞው ሁከት በድምሩ 6 ወጣቶች ህይወታቸውን ማጣታቸውን የገለፁት ሩቶ “ከዚህ በኋላ ከሕግ ውጭ የሚፈጸሙ ግድያዎች እንደማይኖሩም” ቃል ገብተዋል። የሀገሪቱን በጀት በግብር ማሟላት ኬንያ ነፃ የጤና እና የትምህርት ስርዓት እንዲሁም ግብርናን እንድታሳድግ ያስችላታል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሩቶ ተናግረዋል። ማክሰኞ ወደ 214 የሚጠጉ ኬንያውያን ከፖሊስ ጋር በተደረገው “ፍጥጫ” ውስጥ ተሳታፊ እንደነበሩም አንስተዋል። አንድ በድንገተኛ ክፍል ውስጥ የሚገኝ ተሳታፊን ጨምሮ 14 ያህሉ አሁንም በሆስፒታሎች ውስጥ እንደሚገኙ አክለዋል። ኬንያ "የሌሎች ሀገራት ፋብሪካዎች መደብር ሆና መቀጠል አትችልም" ሲሉም ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0