በኒጀር ቦታዋን ያጣችው ዩናይትድ ስቴትስ ከሦስት የአፍሪካ ሀገራት ጋር ትብብሯን ማጠናከር ትፈልጋለች

ሰብስክራይብ
በኒጀር ቦታዋን ያጣችው ዩናይትድ ስቴትስ ከሦስት የአፍሪካ ሀገራት ጋር ትብብሯን ማጠናከር ትፈልጋለች ዩናይትድ ስቴት እየተሳተፈችበት የሚገኝ የአፍሪካ ሀገራት የመከላከያ ኃላፊዎች የሁለት ቀን ኮንፍረንስ በቦትስዋና ዋና ከተማ ጋቦሮኔ እየተካሄደ ነው። በኮንፍረንሱ የ35 አፍሪካ ሀገራት የመከላከያ ኃላፊዎች እና የዩናይትድ ስቴትስ እና ኔቶ ጦር ኃይል ሊቀመንበሮች ተገኝተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሊቀመንበርና የአየር ኃይል ጄኔራል ሲ.ኪው. ብራውን ዩናይትድ ስቴትስ ከኒጀር ጋር ያለው ስምምነት እየተጠናቀቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ወታደራዊ ትብብሯን ለማጠናከር እያሰበች እንደሆነ በአፍሪካዊቷ ሀገር ከማረፋቸው በፊት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን እነዚህ ሀገራት ጋና፣ ቤኒን እና ኮትዲቯርን እንደሚጨምር ለምዕራቡ ዓለም የመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል፡፡ በግንቦት ወር መጨረሻ የኒጀር እና የአሜሪካ ባለስልጣናት የአሜሪካ ወታደሮች በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዘመን መስከረም ወር አጋማሽ ሙሉ በሙሉ ከኒጀር መውጣታቸውን ለማረጋገጥ ተስማምተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0