"ከቅኝ አገዛዝ ነፃ በመውጣት ቅርስን መሰረት ባደረገ ስርዓት ላይ ትኩረት ማድረግ፤" የፓን አፍሪካ ፓርላማ በአፍሪካ የትምህርት ስርዓት ለውጥ እንደሚያስፈልግ አሳሰበ

ሰብስክራይብ
"ከቅኝ አገዛዝ ነፃ በመውጣት ቅርስን መሰረት ባደረገ ስርዓት ላይ ትኩረት ማድረግ፤" የፓን አፍሪካ ፓርላማ በአፍሪካ የትምህርት ስርዓት ለውጥ እንደሚያስፈልግ አሳሰበ የአፍሪካ ህብረት የፓን አፍሪካ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ፎርቹን ቻሩምቢራ "አፍሪካ በርግጥም በፖለቲካ ረገድ "ነጻ ነች"፣ ነገር ግን አሁንም የትምህርት ስርዓታችንን ከቅኝ ግዛት ማላቀቅ እንዳለብን እና የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት ሊደግፍ በሚችለው ቅርስ ላይ መሰረት ያደረገ የትምህርት ስርዓት ዙርያ ትኩረት ማድረግ እንዳለብን አምናለሁ" ሲሉ በፓን አፍሪካ ፓርላማ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። አግባብ የሆኑ፣ ዘላቂ ልማትን የሚያበረታቱ እና በአህጉሪቱ ብልጽግናን ማስፈን የሚያስችሉ ስርአተ ትምህርቶችን ማዘጋጀት ወሳኝ ነውም ብለዋል። "ተምረው፣ ሰልጥነው እና ክህሎት አግኝተው የተሻለ የኑሮ ሁኔታ መፍጠርና የኢኮኖሚ እድገትን ማጎልበት ብቻ ሳይሆን የአህጉራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በአዲስ መልክ እንዲቀርፁ ልንወስዳቸው የሚገቡ አስፈላጊ ጥረቶች አሉ። የጋራ ሀላፊነት ነው" ሲሉ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ፒር ሪቪው ሜካኒዝም አህጉራዊ ሴክሬታሪያት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሜሪ-አንቶይኔት ሮዝ ኳተሬ  አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እ.አ.አ. በ2050 ከ2.3 ቢልየን በላይ ይሆናል ተብሎ ለሚጠበቀው የአፍሪካ ወጣት ህዝብ ጥራት ያለው ትምህርት ማቅረብ አንገብጋቢ መሆኑንም ገልጸዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0