ከኬንያ ጋር ጎረቤት የሆኑ ሀገራት የኢንተርኔት መቆራረጥ ገጥሟቸዋል ተባለ
"የቀጠለው የኢንተርኔት መቆራረጥ በኬንያ እንዲሁም በአጎራባች ሀገራት ኡጋንዳ እና ቡሩንዲ ተፅዕኖ አሳድሯል። መቆራረጡ ተቃውሞ በሚካሄድበት ስፍራ የዘገባ ሽፋንን ሊገድብ ይችላል” ሲል የኢንተርኔት ክትትል አገልግሎት ኔትብሎክስ በኤክስ የትስስር ገፁ አስታውቋል።
ኔትብሎክስ ቀደም ሲል በኬንያ ስለታየው የኢንተርኔት መቆራረጥ ሪፖርት አድርጓል። የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ስርጭትን በተመለከተ የተሰማ ችግር የለም ቢባልም በሰልፉ ዙርያ በሚሰራቸው ዘገባዎች ከኬንያ ባለስልጣናት የፍቃድ እገዳ ማስፈራሪያ እንደደረሰው የሀገር ውስጡ ኬ.ቲ.ኤን ኒውስ አስታውቋል።
በኬንያ የተጨማሪ ግብር ጭማሬውን ለመቃወም ሰኔ 11 የተጀመረው ሰልፍ አሁን በመላ ሀገሪቱ ተዛምቷል። በዋና ከተማው እና በሌሎች ትላልቅ ከተሞች ሰልፎች እየተካሄዱ ነው። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ማሻሻያው ኢኮኖሚውን እንደሚጎዳ እና የኑሮ ውድነትን እንደሚያባብስ እየገለፁ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ከኬንያ ጋር ጎረቤት የሆኑ ሀገራት የኢንተርኔት መቆራረጥ ገጥሟቸዋል ተባለ
ከኬንያ ጋር ጎረቤት የሆኑ ሀገራት የኢንተርኔት መቆራረጥ ገጥሟቸዋል ተባለ
Sputnik አፍሪካ
ከኬንያ ጋር ጎረቤት የሆኑ ሀገራት የኢንተርኔት መቆራረጥ ገጥሟቸዋል ተባለ "የቀጠለው የኢንተርኔት መቆራረጥ በኬንያ እንዲሁም በአጎራባች ሀገራት ኡጋንዳ እና ቡሩንዲ ተፅዕኖ አሳድሯል። መቆራረጡ ተቃውሞ በሚካሄድበት ስፍራ የዘገባ ሽፋንን ሊገድብ ይችላል”... 25.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-25T20:08+0300
2024-06-25T20:08+0300
2024-06-25T22:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий