የሰኔ 18 የጠዋት ዋና ዋና የዓለም ክስተቶች፡-
🟠 እ.አ.አ. በ 2023 እንግሊዝ ለቪዛ ማመልከቻ ክፍያ በተለይም ከእስያ እና ከአፍሪካ ሀገራት 44 ሚሊዮን ፓውንድ ሰበሰባ በኋላ ግን ውድቅ እንዳደረገች አንድ ጥናት ገለፀ። ላጎ ኮሌክቲቭ የተሰኘው የጥናት ቡድን ባደረገው ምርመራ ለአፍሪካውያን ቱሪስቶች የቪዛ ክልከላ መጠን ከ40-70% ደርሷል፣
🟠 በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ልዑክ የኤግሎው ሃይል ወታደራዊ ሰፈርን ለሶማሊያ ብሔራዊ ጦር አስረከበ፣
🟠 የኬንያ ፖሊሶች የሄይቲን የወሮበሎች ሁከት ለመዋጋት ከናይሮቢ ተነሱ፣
🟠 የሩሲያ የሰላም ሀሳቦች የዩክሬንን ግጭት ለማስቆም ተጨባጭ ሁኔታዎችን ያቀርበ ነው ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፣
🟠 የዩክሬን ጦር በማለዳው በሩሲያ ኩርስክ ግዛት በምትገኘው ሱድዛ ከተማ ባካሄደው ድብደባ አንድ ነዋሪ ሲቆስል ሌላ ሰው ደግሞ በልብ ድካም ሆስፒታል መግባቱን የክልሉ ተጠባባቂ ገዥ አስታውቀዋል፣
🟠 በሴቫስቶፖሉ ጥቃት የተጎዱ አራት ህፃናት በከባድ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሞስኮ የሚገኘው የሩሲያ የህፃናት ክሊኒካል ሆስፒታል ገለፀ፣
🟠 የአየር መቃወሚያዎች በሩሲያ ቤልጎሮድ ክልል ላይ 29 እና በቮሮኔዝ ክልል አንድ ድሮኖችን ማውደማቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፣
🟠 ጁልያን አሳንጅ ከብሪታንያ እስር ቤት ተፈቷል። ከአሜሪካ አቃቤ ህግ ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት እሮብ እለት በሳይፓን ደሴት ፍርድ ቤት ቀርቦ ከፊል ጥፋተኝነቱን እንደሚቀበል ምእራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፣
🟠 የቻይናው ቻንግኢ-6 የምርምር ሮቦት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጨረቃ የሩቅ ክፍል የአፈር ናሙና ወደ መሬት አደረሰ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሰኔ 18 የጠዋት ዋና ዋና የዓለም ክስተቶች፡-
የሰኔ 18 የጠዋት ዋና ዋና የዓለም ክስተቶች፡-
Sputnik አፍሪካ
የሰኔ 18 የጠዋት ዋና ዋና የዓለም ክስተቶች፡- 🟠 እ.አ.አ. በ 2023 እንግሊዝ ለቪዛ ማመልከቻ ክፍያ በተለይም ከእስያ እና ከአፍሪካ ሀገራት 44 ሚሊዮን ፓውንድ ሰበሰባ በኋላ ግን ውድቅ እንዳደረገች አንድ ጥናት ገለፀ። ላጎ ኮሌክቲቭ የተሰኘው... 25.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-25T12:24+0300
2024-06-25T12:24+0300
2024-06-25T12:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий