#አጫጭርዜናዎች
የስፑትኒክ ኢትዮጵያ ሰኔ 17 የምሽት ትኩስ ዜናዎችን ይከታተሉ፡-
🟠 በሴቫስቶፖል በደረሰው የሽብር ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ተሳትፎ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሰኞ እለት ገለፁ፣
🟠 ዩክሬን በሴቫስቶፖል ባደረሰችው ጥቃት ሆስፒታል ከገቡት 28 ህጻናት መካከል ሁለቱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳሉ እና ስድስቱ የድንገተኛ ህክምና ክፍል እንደሚገኙ የሩሲያ የህጻናት መብት ኮሚሽነር ማሪያ ሎቮቫ-ቤሎቫ ተናግረዋል፣
🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኪዬቭ በሴቫስቶፖል ካደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት ጋር በተያያዘ በሩሲያ የአሜሪካ አምባሳደር ሊን ትሬሲን ጠርቶ አቤቱታ ማቅረቡን አስታውቋል፣
🟠 በሩሲያ ዳግስታን ሪፐብሊክ በጠመንጃ በተፈፀመ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 20 መድረሱን የክልሉ ጤና ሚኒስቴር ኃላፊ አስታወቁ። እሁድ እለት በደርቤንት እና ማካችካላ ከተሞች ታጣቂዎች በከፈቱት ተከታታይ ጥቃት ቢያንስ 46 ሰዎች ቆስለዋል።
🟠 የአውሮፓ ህብረት ሞስኮ ላይ ለጣለው ማእቀብ ምላሽ ሩሲያ በአውሮፓ ባለስልጣናት ላይ የምትጥለውን የጉዞ ገደብ ዝርዝር እንደምታሰፋ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፣
🟠 የአውሮፓ ህብረት የሃንጋሪን ድምፅ ችላ በማለት ከተወረሱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ወደ ዩክሬን ለመላክ መወሰኑ አሳፋሪ የቀይ መስመር ጥሰት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፒተር ሺጃርቶ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
#አጫጭርዜናዎች
#አጫጭርዜናዎች
Sputnik አፍሪካ
#አጫጭርዜናዎች የስፑትኒክ ኢትዮጵያ ሰኔ 17 የምሽት ትኩስ ዜናዎችን ይከታተሉ፡- 🟠 በሴቫስቶፖል በደረሰው የሽብር ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ተሳትፎ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሰኞ እለት ገለፁ፣ 🟠 ዩክሬን... 24.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-24T20:49+0300
2024-06-24T20:49+0300
2024-06-25T12:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий