ዩክሬን በሩሲያ ሴቫስቶፖል ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት ሁለት ህፃናትን ጨምሮ ቢያንስ ሶስት ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ የከተማው አስተዳዳሪ አስታወቁ

ሰብስክራይብ
ዩክሬን በሩሲያ ሴቫስቶፖል ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት ሁለት ህፃናትን ጨምሮ ቢያንስ ሶስት ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ የከተማው አስተዳዳሪ አስታወቁ እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 100 ተጠግቷል። ኪዬቭ በሩሲያ ሴቫስቶፖል የሲቪል መሰረተ ልማት አውታሮችን በ ኤ.ቲ.ኤ.ሲ.ኤም.ኤስ (ATACMS) ክላስተር ሚሳኤል መምታቷን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። የዩክሬን ጦር ሆን ብሎ ሰዎች የተሰበሰቡበትን ቦታ የጥቃት ዒላማ አድርጓል ሲሉ የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ተናግረዋል። በከተማው የተፈፀመውን ግድያ በተመለከተ ሩሲያ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ምላሽ እንደምትጠይቅ የተናገሩት ቃል አቀባይዋ ሆኖም እነዚህ ድርጅቶች በምእራባውያን ተፅእኖ ስር የወደቁ ናቸው ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0