የማሊ የሽግግር ፕሬዝደንት አሲሚ ጎይታ ፈረንሳይ የማሊን ኢኮኖሚ ​​ለመጉዳት ሀሰተኛ ሴኤፍኤ ፍራንክ ኖቶችን ታትማለች ሲሉ ከሰሱ

ሰብስክራይብ
የማሊ የሽግግር ፕሬዝደንት አሲሚ ጎይታ ፈረንሳይ የማሊን ኢኮኖሚ ​​ለመጉዳት ሀሰተኛ ሴኤፍኤ ፍራንክ ኖቶችን ታትማለች ሲሉ ከሰሱ እ.አ.አ. 1960 በጊኒ ተመሳሳይ ስልት ጥቅም ላይ እንደዋለ ፕሬዝደንቱ በማሊ ሲካሶ ከተማ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል። ይህ አካሄድ ማሊ ላይ የተደቀኑ "ሶስት የሽብር ዓይነቶች" አካል ነው ሲሉም ቀጥለዋል። እነዚህም፦ የትጥቅ ሽብርተኝነት፣ የመገናኛ ብዙሃን ሽብርተኝነት (ውሸት እና የውሸት ዜና "እርስ በርስ ለማጣለት")፣ የኢኮኖሚ ሽብርተኝነት ናቸው ብለዋል። የኢኮኖሚ ሽብርተኝነትን በተመለከተ ኤኮዋስ እ.አ.አ 2022 የጣለውን ማእቀብ ተከትሎ ባማኮ ንግዷን ለማካሄድ ወደ ጊኒ ፊቷን ለማዞር መገደዷን አስታውሰዋል። በጊኒ የማሊ የወደብ ክፍያ በሦስት እጥፍ ከፍ ያለ እንደነበርም አስታውቀዋል። በመጨረሻም የቅኝ አገዛዝ መገበያያ የሆነውን ሴኤፍኤ ፍራንክ በመተው በሀገር ውስጥ መገበያያ መቀየር እንደሚገባ የማሊው መሪ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0