የብሪክስ ሀገራት በጋራ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ እና የአየር ትራንስፖርት ግንኙነትን ለማስፋት በጋራ መስራት አለባቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስትር ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ሰብስክራይብ
የብሪክስ ሀገራት በጋራ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ እና የአየር ትራንስፖርት ግንኙነትን ለማስፋት በጋራ መስራት አለባቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስትር ለስፑትኒክ ተናግረዋል። " የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል  በጣም ጠቃሚ ነው።ምክንያቱም ከሁሉም የአለም ሀገራት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራት እንፈልጋለን። በዚህም የጋራ መግባባትን፣ መከባበርን እንዲሁም ሀገራት ሉዓላዊ እንዲሆኑ ያደርጋል። ከብዙ ሀገራት ጋር የመተባበር እድል ይፈጥራል። " ሲሉ ናሲሴ ጫሊ ተናግረዋል። በብሪክስ ሀገራት መካከል በቱሪዝም መስክ ያለውን ትብብርን ለማጠናከር " የአየር ግንኙነትን እና የቪዛ ተደራሽነትን ማሻሻልን ያስፈልጋል ሲሉ ሚኒስትሯ አሳስበዋል። በ‹‹ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን›› መስክ ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤‹‹እርስ በእርሳችን ፣ ስለ ታሪካችን፣ ባህላችንና የተፈጥሮ ሀብቶቻችን ባወቅን ቁጥር እርስ በርሳችን የመተዋወቃችን ነገር ይጨምራልን። " እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ የብሪክስ ሃገራት በቱሪዝም ዘርፉ ዲጂታላይዜሽን እንዲሁም በዱር እንስሳትና ባህላዊ ቅርሶችን በዘላቂነት መጠበቅ በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት ይችላሉ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0