"ስደተኛ መለያ ነው፤ከስደተኛ ጀርባ ግን ችሎታ ያለው፣ተስፋ ያለው፣ ህልም ያለው ሰው አለ" ሲል አንድ የስደተኛ ተሟጋች ይናገራል።

ሰብስክራይብ
"ስደተኛ መለያ ነው፤ከስደተኛ ጀርባ ግን ችሎታ ያለው፣ተስፋ ያለው፣ ህልም ያለው ሰው አለ" ሲል አንድ የስደተኛ ተሟጋች ይናገራል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን ትላንት ሐሙስ ተከብሯል፤በአስገዳጅ ሁኔታ የመኖሪያ አካባቢያቸውን ጥለው የሚሰደዱ ሰዎችን ለማሰብ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበር ቀን ነው። በዚህ አጋጣሚ ስፑትኒክ የአሽደን በጎ አድራጎት ድርጅት የስደተኞች ተሟጋች እና ተመራማሪ አንድሂራ ዩሲፍ ካራን አነጋግሯል። ከሱዳን የመጣች ስደተኛ ነች፤አሁን በኬንያ የምትኖረው እና የስደተኞች እና የተፈናቀሉ ዜጎችን መብት ለማሻሻል ከሀገር አቀፍ እና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ትሰራለች። እሷ እንደምትለው፣ ስደተኞች ከሚገጥሟቸው ፈተናዎች አንዱ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ቶሎ መዋሃድ ነው።ከዚህ ችግር ጋር ተያይዞ የተለያዩ ሀገራት የተለያዩ መፍትሄዎችን አቅርበዋል ትላለች። "ኡጋንዳ በአሁኑ ጊዜ ከኬንያ ጋር የስደተኞች ፖሊሲን በተመለከተ ግልፅ በሆነ መንገድ ከማህበረሰቡ ጋር የሚዋሀዱበት መንገድ ማረጋገጥ ችላለች፣ የሸሪአ እቅድን እና የስደተኞች አስተዳደር አዲስ መመሪያን በመተግበር ስደተኞቹ ከካምፕ ወጥተው ወደሚሄዱባቸው ሀገራት በተቀናጀ መልኩ በመሥራት ላሉበት ሀገር የኢኮኖሚ አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ያስችላል" ስትል የስደተኞቹ ተሟጋች አፅንዖት ተናግራለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0