ቻድ የእንቅልፍ በሽታን በማጥፋት በአለም 51ኛዋ ሀገር ሆናለች።

ሰብስክራይብ
ቻድ የእንቅልፍ በሽታን በማጥፋት በአለም 51ኛዋ ሀገር ሆናለች። "የቻድ መንግስት፣ የጤና ባለሙያዎች እና የቻድ ህዝቦች ፤ የእንቅልፍ በሽታ በመባል የሚታወቀውን በሌላ አጠራር አፍሪካዊ ትራይፓኖሶሚያሲስን በማጥፋት እንኳን ደስ አላችሁ። ቻድ ቢያንስ አንድ ችላ የተባለ የትሮፒካል አካባቢ በሽታን ካስወገዱ ሃገራት ተረታ መቀላቀሉን ማየት በጣም ደስ ይላል።ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ ተናግረዋል። የእንቅልፍ ሕመም መጀመሪያ ላይ ጉንፋን መሰል ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል፤ ነገርግን በኋላ ላይ የባህሪ ለውጥ፣ግራ መጋባት፣የእንቅልፍ ዑደት መቆራረጥ አልፎ ተርፎም ኮማ ውስጥ ሊከት የሚችል እና በአብዛኛው ለሞት ሊዳርግ ሁሉ የሚችል በሽታ ነው። እስካሁን ድረስ፣አፍሪካዊ ትራይፓኖሶማያሲስ ጋምቢሴስ በመባል የሚታወቀውን ይህ በሽታ  በአህጉሪቱ ሰባት ሀገሮችመጥፋቱን የዓለም የጤና ድርጅት አረጋግጧል። እነዚህም፦ 🟠 ቶጎ (2020) 🟠 ቤኒን (2021) 🟠 ኮትዲቯር (2021) 🟠 ኡጋንዳ (2022) 🟠 ኢኳቶሪያል ጊኒ (2022) 🟠 ጋና (2023) 🟠 ቻድ (2024) ናቸው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0