ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በማዕድን እና ጂኦሎጂካል ፍለጋ ያላቸውን ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማጠናከር እየሠሩ ነው

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በማዕድን እና ጂኦሎጂካል ፍለጋ ያላቸውን ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማጠናከር እየሠሩ ነው በዋና አማካሪ ዲሚትሪ ኦሌይኒክ የተመራ የሩሲያ የማዕድን ቁፋሮ አስተዳደር ኤጀንሲ የልኡካን ቡድን ለስራ ጉብኝት በትላንት እለት ኢትዮጵያ መግባቱን የኤጀንሲው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል። ስብሰባው ያተኮረው ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በጂኦሎጂ እና በማዕድን ፍለጋ ዙሪያ የሚያደርጉትን ትብብር ውጤት እና የወደፊት ተስፋ በመገምገም፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እና የኢትዮጵያን የማዕድን ሃብት የማልማት እድሎችን ለማሳየት እንደሆነ ተገልጿል። "ከኢትዮጵያ  ጋር በጂኦሎጂ እና በከርሰ ምድር ሀብት አጠቃቀም ዙሪያ ያለንን ትብብር በተደራጀ መልኩ መሥራት እንቀጥላለን።ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እ.አ.አ ታህሣሥ 20 በአዲስ አበባ የተካሄደው የሩሲያና የኢትዮጵያ የንግድ ፎረም ነው። ይህ ደግሞ የሆነው በሩስያ እና በኢትዮጵያ መንግስታት፤በሳይንሳዊ ምርምር፣ በንግድ እና በከርሰ ምድር አጠቃቀም ዙሪያ በተቋቋመው ኮሚሽን አማካኝነት ነው። ይህ ኮሚሽን ለሁለትዮሽ ግንኙነቶች መዳበር ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0