ሩሲያ በሊቢያ የውጭ ሃይሎችን ከወታደራዊ ቡድኖችን ጋር የማገናኘት እቅድ እንዳሳሰባት በተመድ የሀገሪቱ ምክትል አምባሳደር ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ በሊቢያ የውጭ ሃይሎችን ከወታደራዊ ቡድኖችን ጋር የማገናኘት እቅድ እንዳሳሰባት በተመድ የሀገሪቱ ምክትል አምባሳደር ተናገሩ ሩሲያ በሊቢያ ግጭት ከሀገሪቱ ውጭ ያሉ ሀይሎት በሀገሪቱ ምስራቅ እና ምዕራብ የሚገኙ ክፍሎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ የሚያገናኙ የግል ወታደራዊ ኩባንያዎችን ለማሰልጠን እና ለማስታጠቅ ያቀዱትን እቅድ፤ አሳሳቢ ነው ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ ምክትል አምባሳደር አና ኢቭስቲኒቫ ማክሰኞ ዕለት ገለፀዋል። "ከዚህም በላይ የውጪ ሃይሎት የግል ወታደራዊ ኩባንያዎችን ለማቋቋም፣ ለማሰልጠን እና ለማስታጠቅ ያላቸውን ግልጽ ያልሆኑ ዕቅዶችን በተመለከተ መረጃ መውጣቱ እና የሊቢያ ተዋጊዎች በግል ወታደራዊ ኩባንያዎች ታግዘው የሊቢያ ድንበር ጭምር በጋራ እንዲጠብቁ እና በሊቢያ ምዕራባዊ እና ምስራቃዊ አካባቢ ያሉ ተዋጊዎች አንድ ሊያደርጉ ነው መባሉ አሳሳቢ ነው "ሲሉ አምባሳደሩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  ፀጥታው ምክር ቤት በሊቢያ ላይ ባደረገው ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ኢቭስቲኒቫ እንዳሉት ሩሲያ እንደዚህ ያሉ እቅዶች ለብሔራዊ የሊቢያ ጦር አይጠቅሙም፤ ለተወሰኑ የውጭ ሀገራት ብሄራዊ ጥቅም እንጂ ሲሉ ተናገረዋል። ሩሲያ በሊቢያ ያሉ የውጭ ተዋጊዎች ጠቅልለው መውጣት አለባቸው በማለት ብዙ ጊዜ ተከራክራለች እና ይህ አሁንም ደረጃ በደረጃ መደረግ ያለበት ወሳኝ ግብ ነው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0