ዩኔስኮ በአፍሪካ በሚገኙ ብሄራዊ ፓርኮች አካባቢ የሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተባባሪ ነው ተባለ

ሰብስክራይብ
ዩኔስኮ በአፍሪካ በሚገኙ ብሄራዊ ፓርኮች አካባቢ የሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተባባሪ ነው ተባለ ለዓመታት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በዩኔስኮ በዓለም ቅርሶች ተብለው በተመዘገቡ ቦታዎች ላይ የሚፈጸሙ ህገ-ወጥ ማፈናቀልን፣ ማሰቃየትን፣መደፈርን እና ግድያንን ችላ በማለት ሲተች ይሰማል።ተቺዎች ደካማ የማስፈጸም አቅም፣ህዝብን የመቆጣጠር ፍላጐት እና ውስጣዊ የፖለቲካ ሥርዓትን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል በቅርቡ ባወጣው ዘገባ ዩኔስኮ በታንዛኒያ ንጎሮንጎሮ እና በኮንጎ ኦድዛላ-ኮኩዋ በመሳሰሉት የአካባቢው ተወላጆች ላይ የሚደረገውን ህገወጥ ማፈናቀል እና በደል ይደግፋል ብሏል። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶቹ ዩኔስኮ በደካማ አፈጻጸም የተነሣ እና በፖሊሲ ጉዳዮች ሳቢያ እነዚህ ጥሰቶች ቢኖሩም የዓለም ቅርስነት ደረጃን ሰጥቷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0