የኢትዮጵያ የብሪክስ"አዲሱ ልማት ባንክ" አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ መገኘቱን አምባሳደር ነብዩ ተድላ ገለፁ
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፤ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲሱ ልማት ባንክ አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ የፖለቲካ ድጋፍ ከተለያዩ አገሮች ማገኘቷን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በሩሲያ የብሪክስ ስብሰባዎችና ተጎዳኝ መድረኮች ላይ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጓን ጠቅሰው ፤የብሪክስ አገራት የብሔራዊ ተወካዮችና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተሳትፎ ማድረጓን ገልጸዋል።
በመድረኩ ኢትዮጵያን ጨምሮ አዳዲስ የብሪክስ አባል አገራት የብሪክስ "አዲሱ የልማት ባንክ " አባል እንዲሆኑ ድጋፍ እንዲሰጣቸው ተቀምጧል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኩል እንደ አገር በብሪክስ ተሳትፎዋ ያላትን የጎላ ሚና ለማሳደግ የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ መቆየቷን ማብራራታቸውን ገልጸዋል።
ሩሲያ በነበረው ቆይታ ከቻይና፣ ከብራዚል፣ከደቡብ አፍሪካና ሩሲያ ጋር የተደረጉ የተናጠል ውይይቶች መደረጉን እናሀገራቱ ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲሱ ልማት ባንክ አባል ለመሆን ላቀረበችውን ጥያቄ ድጋፍ እንደሚሰጡ ማረጋገጣቸውን ቃልአቀባዩ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ የብሪክስ"አዲሱ ልማት ባንክ" አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ መገኘቱን አምባሳደር ነብዩ ተድላ ገለፁ
የኢትዮጵያ የብሪክስ"አዲሱ ልማት ባንክ" አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ መገኘቱን አምባሳደር ነብዩ ተድላ ገለፁ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ የብሪክስ"አዲሱ ልማት ባንክ" አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ መገኘቱን አምባሳደር ነብዩ ተድላ ገለፁ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፤ኢትዮጵያ የብሪክስ... 20.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-20T14:39+0300
2024-06-20T14:39+0300
2024-06-20T15:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያ የብሪክስ"አዲሱ ልማት ባንክ" አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ መገኘቱን አምባሳደር ነብዩ ተድላ ገለፁ
14:39 20.06.2024 (የተሻሻለ: 15:20 20.06.2024)
ሰብስክራይብ