የአፍሪካ ሚኒስትሮች በአህጉሪቱን ልማት እና እድገትን ለማምጣት የአርቴፊሻል ኢንተጀንስ ስትራቴጂን መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሚኒስትሮች በአህጉሪቱን ልማት እና  እድገትን ለማምጣት የአርቴፊሻል ኢንተጀንስ ስትራቴጂን መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። የአህጉራዊው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ስትራቴጂ የአፍሪካን የልማት ግቦችን ለማሳካት ፣የህዝቦቿን አኗኗር ለማሻሻል እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ለአፍሪካ ሀገራት አቅጣጫ ይሰጣል ፣እንዲሁም ለሥነ-ምግባር አሠራሮች ፣ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ እና ሊኖሩ የሚችሉ ጥቅምን ለማሳደግ እንደሚረዳ የአፍሪካ ህብረት በማለት ተናግሯል። ከዚህ ባለፈም አፍሪካ በ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የቀረቡትን ጉልህ እድሎች ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ቅድሚያ እንድትሰጥ እና እርምጃ እንድትወስድ አጽንኦት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቅሷል። ስትራቴጂው አፍሪካን ያማከለ፣ ልማት ላይ ያተኮረ እና ህዝቦቿን ያሳተፈ አካሄድ እንዲከተል እና የአፍሪካ ሀገራት በመሠረተ ልማት፣ በሰው ሃይል ልማትካ፣ የመረጃ ቋቶችን ማበልፀግ፣ በፈጠራ ስራዎችዎ ፣ በትምህርት እና ክህሎት፣ ጤና ጥበቃ፣ ግብርና፣ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ዘርፎች የአፍሪካ ሀገራትን የአርቴፊሻል ኢንተጀንስ አቅም ማፋጠን እንደሚያስፈልግ ያነሳል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0