የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) ሶማሊያ ሙሉ በሙሉ ከህብረቱ ጋር የምትቀላቀልበትን ዝርዝር እቅድ አቅርቧል።
ሶማሊያ በበኩሏ በአሁኑ ወቅት በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ባለው ወሳኝ አህጉራዊ ስብሰባ ላይ በንቃት በመሳተፍ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ለመሆን ቁርጠኝነቷን አሳይታለች።
"የዛሬው ስብሰባ በዚህ ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍን ላይ መሆናችንን ያሳያል፤የሶማሊያን አባልነት ሂደቶችን ከክልላዊ ማዕቀፎች ጋር በማጣጣም ሁሉን አቀፍ ውህደትን ለማረጋገጥ መሠረት የምንጥልበት ነው ሲሉ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ዋና ፀሐፊ ቬሮኒካ ንዱቫ ተናግረዋል።
ፍኖተ ካርታው ሶማሊያ ከማህበረሰቡ የጉምሩክ ዩኒየን እና ከጋራ ገበያ ጋር ለመዋሃድ የምትተገብረውን ጉዳዮች የጊዜ ሰሌዳ እና ፖሊሲ ይዘረዝራል።
"ፍኖተ ካርታው በብሔራዊ እና በማህበረሰብ ተኮር ተነሳሽነት የተከፋፈሉ አስፈላጊ ተግባራትን ይዘረዝራል። እነዚህም የሶማሊያ የህግ ማዕቀፎችን ከተቀመጡ ክልላዊ ደረጃዎች ጋር ማመጣጠን እና ምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ፕሮግራሞች እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጠንካራ ተሳትፎ ማረጋገጥን ያካትታሉ" ሲሉ ንዱቫ አክለዋል።
ምንም እንኳን የተቀመጡ የጊዜ ሰሌዳዎች ባይኖሩም የሶማሊያ ባለስልጣናት ለመዋሃድ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በህብረቱ ውስጥ ካሉት ስምንቱ አባል ሀገራት አምስቱ ብቻ ሙሉ ለሙሉ ውህደቱን የተቀላቀሉ ሲሆን በዚህ ም እርስ በርስ በነፃነት ለመገበያየት አስችሏቸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) ሶማሊያ ሙሉ በሙሉ ከህብረቱ ጋር የምትቀላቀልበትን ዝርዝር እቅድ አቅርቧል።
የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) ሶማሊያ ሙሉ በሙሉ ከህብረቱ ጋር የምትቀላቀልበትን ዝርዝር እቅድ አቅርቧል።
Sputnik አፍሪካ
የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) ሶማሊያ ሙሉ በሙሉ ከህብረቱ ጋር የምትቀላቀልበትን ዝርዝር እቅድ አቅርቧል። ሶማሊያ በበኩሏ በአሁኑ ወቅት በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ባለው ወሳኝ አህጉራዊ ስብሰባ ላይ በንቃት በመሳተፍ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ... 20.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-20T12:10+0300
2024-06-20T12:10+0300
2024-06-20T12:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) ሶማሊያ ሙሉ በሙሉ ከህብረቱ ጋር የምትቀላቀልበትን ዝርዝር እቅድ አቅርቧል።
12:10 20.06.2024 (የተሻሻለ: 12:40 20.06.2024)
ሰብስክራይብ