ሱዳን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ጉዳይ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት ተጋጩ
ሱዳን እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (UAE) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቃላት ጦርነት ውስጥ የገቡት የሱዳን መንግስት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF)የጦር መሳሪያ ታቀርባለች በሚል ውንጀላ ሳቢያ ነው።
የሱዳኑ አምባሳደር አልሃሪት መሀመድ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በምታቀርበው የጦር መሳሪያ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዲፈፀም አያደረገች ነው ሲሉ ጉዳዩን ለአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለማቅረብ ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።
" ከኤሚሬትስ በሚቀርብ የጦር መሳሪያ በመታገዝ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ሆን ተብሎ እና በተደራጀ መንገድ በመንደሮችን እና ከተሞችላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈጸመ ነው" ብለዋል አምባሳደር መሀመድ።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አምባሳደር መሀመድ አቡሻሃብ ክሱን ሀሰት ሲሉ አጣጥለው ፤ ክሱ በትክክል የተፈፀሙ ጥሰቶች ትኩረት እንዳይሰጣቸው ለማድረግ የቀረበ ነው ሲሉ ተከራክረዋል።
"ግጭቱን እና የዜጎችን ስቃይ ለማስቆም ከፈለጉ ለምን ወደ ጅዳ ስምምነትን አይመጡም? ለምንድነው እርዳታ የሚከለክሉት? ምንድነው የምትጠብቁት?" ሲሉ አቡሻሃብ ከጎናቸው ለተቀመጠው የሱዳን አምባሳደር ምላሽ ሰጥተዋል።
በስብሰባው ላይ የመንግስታቱ ድርጅት በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ በሆነችው በኤል ፋሸር፣ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከበባ ውስጥ ያሉ ዜጐች ተጨማሪ አሰቃቂ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለመከላከል፣ ወሳኝ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን ለመጠበቅ እና የዜጎችን ስቃይ ለመቅረፍ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ተጠይቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሱዳን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ጉዳይ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት ተጋጩ
ሱዳን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ጉዳይ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት ተጋጩ
Sputnik አፍሪካ
ሱዳን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ጉዳይ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት ተጋጩ ሱዳን እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (UAE) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቃላት ጦርነት ውስጥ... 20.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-20T11:33+0300
2024-06-20T11:33+0300
2024-06-20T12:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሱዳን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ጉዳይ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት ተጋጩ
11:33 20.06.2024 (የተሻሻለ: 12:20 20.06.2024)
ሰብስክራይብ