የሰኔ 12 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሰኔ 12  ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 ቭላድሚር ፑቲን እና ኪም ጆንግ ኡን በሀገራቱ ላይ ጥቃት ሲሰነዘር በጋራ መመከትን ጨምሮ ፤አጠቃላይ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል። 🟠 ሲሪል ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል። 🟠 የሩስያ ፓርላማ ኮሚሽን የጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽሕፈት ቤት እና የፌደራል ደኅንነት አገልግሎት የዩክሬን ጦር ኃይሎችን፣ የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት እና የዩክሬን ዋና የመረጃ ዳይሬክቶሬት በአሸባሪ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ ሐሳብ አቅርቧል። 🟠 በሩሲያ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን ሮሳቶም ላይ የተጣለው ማዕቀብ በኒውክሌር ደህንነት ላይ አሉታዊ ውጤት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ኃላፊ ራፋኤል ግሮስሲ ተናግረዋል። 🟠 የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በዩክሬን ግጭት ዙሪያ በስዊዘርላንድ የተካሄደውን ስብሰባ ዙሪያ በመደበኛነት ግንኙነት አላቸው በሚል ከስዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተሰነዘውን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል። 🟠 የጀርመኑ ምክትል ቻንስለር ሮበርት ሃቤክ ሁለት ዘመዶች የናዚ ጀርመን መኮንኖች እንደነበሩ የጀርመኑ ቡንቴ መጽሔት ዘግቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0