ሩዋንዳ ከዩክሬን የሰላም ጉባኤ መግለጫ ፊርማዋን አንስታለች።

ሰብስክራይብ
ሩዋንዳ ከዩክሬን የሰላም ጉባኤ መግለጫ ፊርማዋን አንስታለች። በስዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ በወጣው ዝርዝር መሰረት ሩዋንዳ የዩክሬን ሰላም ስብሰባ የመጨረሻ መግለጫ ላይ ፊርማዋን የሻረች ሶስተኛዋ ሀገር ሆናለች። ከሩዋንዳ መውጣት ቀደም ብሎ ኢራቅ እና ዮርዳኖስም ፊርማቸውን እንዳነሱ  መግለጻቸው ይታወቃል። ከ91 ተሳታፊ ሀገራት 74ቱ በዩክሬን ግጭት ዙሪያ የተካሄደውን የመሪዎች ጉባኤ የመጨረሻ ውጤት መግለጫን አጽድቀዋል። መግለጫው "ህያው ሰነድ"ሲሆን ሀገራት በማንኛውም ጊዜ ፊርማቸውን ማኖር ወይም ማንሳት እንደሚችሉ የስዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0