ሞስኮ እና ፒዮንግያንግ አጠቃላይ የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ
ሞስኮ እና ፒዮንግያንግ  አጠቃላይ የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ ዛሬ የተፈረመውት ሥምምነት ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል ፤በዚህ ሰነድ ውስጥ ካሉት ወገኖች በአንዱ ላይ ወረራ በሚፈፀምበት ወቅት በጋራ ለመመከት የሚያስችል ነው። ሁለቱ መሪዎች ከስምምነቱ ፊርማ በተጨማሪ የሚከተሉትን ቁልፍ መግለጫዎች ሰጥተዋል። 🟠 ሞስኮ በስምምነቱ መሰረት ከሰሜን ኮሪያ ጋር ወታደራዊ እና ቴክኒካል ትብብር ማድረግን አይከለክልም 🟠 በሞስኮ እና በፒዮንግያንግ መካከል የተፈረመው ስምምነት በባህሪው ሰላማዊ እና መከላከል ላይ ያተኮረ ሲሆን አዲስ የብዝሃ ዓለም አቀፍ ሥርዓት በቶሎ እንዲፈጠር ያስችላል። 🟠 ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት "ወደ አዲስ ደረጃ" ያሳድጋል።ይህም በፖለቲካ፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ በባህላዊና ሰብአዊነት መስኮች እንዲሁም በፀጥታ ዘርፍ ላይ ይሠራል። 🟠 ሩሲያም ሆነች ሰሜን ኮሪያ ነፃ የውጭ ፖሊሲዎችን በመከተል የውጭ ኃይሎችን ጫና አንደማይቀበሉ በግልፅ አስቀምጠዋል። 🟠 ሞስኮ እና ፒዮንግያንግ ምዕራባውያን የበላይነታቸውን ለማስቀጠል ማዕቀብን እንደመሳሪያ የሚጠቀሙበትን መንገድ መቃወማቸውን ይቀጥላሉ። 🟠 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኮሪያ ላይ በአሜሪካ አማካኝነት የጣለባትን ማዕቀብ እንደገና ሊያጤነው ይገባል ብለዋል። 🟠 ሩሲያ ለሰሜን ኮሪያ  በጣም ታማኝ ጓደኛ እና አጋር ናት ፣ ፑቲን ደግሞ የኮሪያ ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቦታጋያለው ወዳጅ ነው። 🟠 Uገራቱ በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት እያዳበሩ ነው። 🟠 በግብርና፣ በባህል እና በሰብአዊ ጉዳዮች ያላቸው ግንኙነት እያደገ ነው።ሀገራቱ በቱሪዝም ዘርፍም ትብብር ለማድረግ ተስማምተዋል። 🟠 ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ "ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ብዝሃ ዓለም አቀፉ ስርአት የመፍጠር ሀሳብን በአበክረው ይደግፋሉ።" 🟠 ሞስኮ እና ፒዮንግያንግ ለአለም አቀፉ ወታደራዊ-ፖለቲካዊ ውጥረት መባባስ መሰረታዊ መንስኤዎች ላይ ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0