ሃሰተኛ መረጃን ለመዋጋት የወቅቱን የሚዲያ ባህሪ በአግባቡ መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ገለጹ

ሰብስክራይብ
ሃሰተኛ መረጃን ለመዋጋት የወቅቱን የሚዲያ ባህሪ በአግባቡ መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ገለጹ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ የልዑክ ቡድን በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። “ኃላፊነት የተሞላበት የመረጃ ስርጭት ፍትሐዊ የዓለም ስርዓትን ከመገንባት አንጻር” በሚል ርዕስ በተስተናገደው የፎረሙ ክፍል ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አዲሱ አረጋ በአሁኑ ወቅት ያልተረጋገጠ፤ የተዛባና ሃሰተኛ መረጃ ሃላፊነት በጎደለው መልኩ በፍጥነት ሲሰራጭ ይታያል ብለዋል። ችግሩን ለመቋቋም ቴክኒካዊ መፍትሔ ብቻ ሳይሆን የሚዲያ ባህርያትን መረዳት እንደሚገባ አስረድተዋል። ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ያከበረ ሃሰተኛ የመረጃ ስርጭቶችን የሚከላከሉ የተጠያቂነት የሕግ ማዕቀፎችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነም አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር በጋራ በመስራት የዲጂታላይዜሽንን የለውጥ አቅም ለመጠቀም ቁርጠኛ መሆኗን የገለጹት አዲሱ አረጋ በጋራ ፍትሃዊ፣ አካታችና ስኬታማ ዓለምን እንገንባ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0