ማሊ በሩሲያ ድጋፍ ወታደራዊ አቅሟን ለማሳደግ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ

ሰብስክራይብ
ማሊ በሩሲያ ድጋፍ ወታደራዊ አቅሟን ለማሳደግ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ የማሊ አላማ በሩሲያ ድጋፍ ወታደራዊ አቅሟን በፍጥነት ማሳደግ ሲሆን ሀገራቱ በወታደራዊ መሳሪያ ግዥ መርሃ ግብር ላይ እየተወያዩ እንደሆነ የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላዬ ዲዮፕ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። በምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ የሩስያ የልዑካን ቡድን ባማኮን በቅርቡ ጎብኝቷል። እንደ ዲዮፕ ገለጻ ይህ ጉብኝት ማሊ "ወታደራዊ እና የመከላከያ አቅሟን ከፍ የማድረግ" እቅዷን የማፋጠን ፍላጎቷን ያሳያል፡፡ "ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ አጋርነት ለማጠናከር የሚደረገው ውይይት አካል ነው። ይህ መሰረት ያደረገው የማሊ የመከላከያ እና የፀጥታ ኃይሎች የውግያ አቅምን በማጠናከር ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ እንዲሁም የወታደራዊ መሳሪያዎች ግዥ ፕሮግራም ላይ ነው” ሲሉ ዲዮፕ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0