የሩስያ ንብረቶችን መውረስ ህገወጥ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን የሚጻረር ነው ሲሉ የኬንያው ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የሩስያ ንብረቶችን መውረስ ህገወጥ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን የሚጻረር ነው ሲሉ የኬንያው ፕሬዝዳንት ተናገሩ "የሩሲያ ንብረቶችን በአንድ ወገን ውሳኔ መውረስ [...] ሕገ-ወጥ፣ ተቀባይነት የሌለው እና የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን የሚያሳንስ ነው በተለይም በነጻነት፣ ፍትህ፣ ዲሞክራሲ እና በህግ የበላይነት ለሚያምኑቱ" ሲሉ በስዊዘርላንድ የዩክሬን ኮንፈረንስ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል። የዩክሬን ጦርነት የማዳበሪያ ዋጋ እንዲጨምርና የአቅርቦት መዘግየት በመፍጠር የኬንያ ገበሬዎች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳሳደረ ያነሱት የኬንያው ፕሬዝዳንት የሰላም ጥሪ አቅርበዋል። የኬንያው መሪ “የዩክሬን ጦርነት ተካፋይ ወገኖች መተማመን የሚያሳዩበት፣ ግትር አመለካከቶችን የሚተውበት እና አቋማቸውን የሚያለዝቡበት ጊዜ አሁን ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። የሰላማዊ ድርድር ጥያቄ ከተነሳ "ሩሲያ [በድርድሩ] ጠረጴዛ ዙርያ ልትኖር ይገባል" ሲሉም አክለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0