ብሪክስ በ15 ዓመታት ውስጥ ከኢኮኖሚያዊ ትብብር ወደ ፖለቲካ ሃይል እንደተለወጠ ብራዚላዊ ባለሙያ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ብሪክስ በ15 ዓመታት ውስጥ ከኢኮኖሚያዊ ትብብር ወደ ፖለቲካ ሃይል እንደተለወጠ ብራዚላዊ ባለሙያ ተናገሩ ብሪክስ በቆየባቸው ዓመታት ፕሮጀክቶች የሚቀረፁብት የውይይት ቡድን እና አሁን ላሉ ዓለም አቀፍ አደረጃጀቶች ስልታዊ አማራጮች የሚፈጠሩበት ሆኗል ሲሉ በብራዚል የካፒታል ገበያ ኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሆሴ ኒሜየር ለስፑትኒክ ተናግረዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ ስብስቡን ለመቀላቀል የሚፈልጉ ሀገሮች ቁጥር እየጨመረ መሄዱን ይቀጥላል። "የዓለም ስርአት ያልተረጋጋ ሆኗል። ብሪክስ አዳዲስ ሀገራትን መቀላቀሉ አይቀርም ይህም እርስ በርስ መስተጋብርን በመፍጠር ለዓለም አቀፍ ስርዓት የበለጠ ሚዛን እና ስምምነት ያመጣል። በአሁኑ ወቅት በዚህ ጉዳይ ላይ የጋራ መግባባት የለም" ሲሉ ባለሙያው ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0