የሰኔ 10 ምሽት ዋና ዋና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፡-
🟠 የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በዓለም አቀፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም ባስተላለፉት መልእክት መጪው ዘመን ከቅኝ ግዛት እና ከአዲስ የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲዎች የጸዳ መሆን አለበት አሉ።
🟠 በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ 5 ፓርቲዎች የብሔራዊ አንድነት መንግስትን እንደተቀላቀሉ የአፍሪካ ኤ.ኤን.ሲ አስታወቀ።
🟠 ፈረንሳይ በምዕራብ እና ማእከላዊ አፍሪካ ያሏትን ወታደሮች ወደ 600 ለመቀነስ አቅዳለች ሲል ኤኤፍፒ ዘገበ።
🟠 ቭላድሚር ፑቲን ሰሜን ኮሪያን እና ቬትናምን ከሰኔ 11-13 እንደሚጎኙ ክርምሊን አስታወቀ፡፡
🟠 የክሬምሊን ቃል አቀባይ በስዊዘርላንድ የተካሄደው የዩክሬን ኮንፈረንስ ስኬት ወደ ዜሮ እየተቃረበ ነው አሉ።
🟠 የአውሮፓ ኅብረት ለኪየቭ የሚሰጠውን ዕርዳታ ከሙስና እና ምዝበራ የሚከላከል ኮሚሽን አቋቋመ፡፡
🟠 የሮናልድ ሬገን ኢንስቲትዩት ባከናወነው አስተያየት መስጫ መሰረት አንድ ሶስተኛ አቅራብያ (32%) አሜሪካውያን ወታደራዊ እርዳታ ወደ ዩክሬን መላክን ይቃወማሉ።
🟠 የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ተስክ የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ካጃ ካላስ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች ከፍተኛ ተወካይ ዕጩነትን ሀገራቸው እንደምትደግፍ ገለፁ፡፡
🟠 የዩክሬን ጦር በሩሲያ ቤልጎሮድ አንድ መንደር ላይ ባካሄደው ጥቃት 3 ንፁሀን ዜጎች መቁሰላቸውን የክልሉ አስተዳዳሪ አስታወቁ።
🟠 ከአዘርባጃን ጋር ድንበር በሚከለልበት ወቅት የግዛት ልውውጥ ጉዳይ ከተነሳ አርሜኒያ ህዝበ ውሳኔ ማካሄድ አለባት ሲሉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።
🟠 ኤለን መስክ ኩባንያው ኒውራሊንክ በሰው አንጎል ውስጥ የሚቀብረው ቺፕ ወደፊት የሞባይል ስልኮችን ይተካል ብሎ እንደሚያምን ተናገረ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሰኔ 10 ምሽት ዋና ዋና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፡-
የሰኔ 10 ምሽት ዋና ዋና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፡-
Sputnik አፍሪካ
የሰኔ 10 ምሽት ዋና ዋና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፡- 🟠 የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በዓለም አቀፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም ባስተላለፉት መልእክት መጪው ዘመን ከቅኝ ግዛት እና ከአዲስ የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲዎች የጸዳ መሆን አለበት አሉ። 🟠 በደቡብ አፍሪካ... 17.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-17T20:13+0300
2024-06-17T20:13+0300
2024-06-17T20:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий