በማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ቺሊማ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ አራት ሰዎች ተገደሉ
የማላዊ ሟች ምክትል ፕሬዝዳንት የቀብር ሥነ ሥርዓት አጃቢ ተሽከርካሪ እሁድ ምሽት በአንድ መንደር ሐዘንተኞችን ገጭቶ 4 ሰዎች ሲገድል 12 የሚሆኑት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ፖሊስ ተናግሯል።
ባለፈው ሳምንት በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ሳሎስ ቺሊማን አስከሬን ከሚያጅቡ መኪኖች ውስጥ አንደኛው ነው፡፡ ተሽከርካሪው በማዕከላዊ ማላዊ በምትገኘው ንቼዩ መንደር በተሰበሰበው ሕዝብ ላይ ደረማምሶ እንደገባ ተሰምቷል።
"በደረሰው ጉዳት ሁለት ሴት እና ሁለት ወንድ እግረኞች ከፍተኛ የሆነ የጭንቅላት ጉዳት እና በርካታ ስብራት ደርሶባቸው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ህይወታቸው አልፏል" ሲል ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የምክትል ፕሬዝዳንቱን የሬሳ ሳጥን ለማየት በየመንገዱ ተሰልፈው ነበር። አንድ የዓይን እማኝ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት ተሽከርካሪው ከህዝቡ ለመራቅ ሲሞክር ወደ ተሰበሰቡት ሰዎች ደርምሶ ሊገባ ችሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ቺሊማ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ አራት ሰዎች ተገደሉ
በማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ቺሊማ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ አራት ሰዎች ተገደሉ
Sputnik አፍሪካ
በማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ቺሊማ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ አራት ሰዎች ተገደሉ የማላዊ ሟች ምክትል ፕሬዝዳንት የቀብር ሥነ ሥርዓት አጃቢ ተሽከርካሪ እሁድ ምሽት በአንድ መንደር ሐዘንተኞችን ገጭቶ 4 ሰዎች ሲገድል 12 የሚሆኑት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ... 17.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-17T19:21+0300
2024-06-17T19:21+0300
2024-06-17T19:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий