ሩሲያ ሐምሌ 9 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚካሄደው ስብሰባ አዲስ የዓለም አቀፍ "የደህንነት ቀመር" ርዕስን እንደምታነሳ ገለፀች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ሐምሌ 9 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚካሄደው ስብሰባ አዲስ የዓለም አቀፍ "የደህንነት ቀመር" ርዕስን እንደምታነሳ ገለፀች በተባበሩት መንግሥታት የሩስያ ቋሚ ተወካይ ቫሲሊ ንቤንዝያ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለ መጪው የዓለም ስርዓት ስትራቴጅያዊ ውይይት ለማካሄድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡ "የሁሉም ሀገራት ጥቅም ከግምት ውስጥ የሚገባበት እውነተኛ ፍትሃዊ የዓለም ስርዓት መለኪያዎች፣ ተመድ በሂደቱ ላይ ስለሚኖረው ሚና፣ የድርጅቱን አመኔታ እና በዓለም አቀፉ ድርጅት ውስጥ ገንቢ ትብብር ወደነበረበት መመለስን እንዲሁም አዲስ "የደህንነት ቀመር"ን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውይይት ለማድረግ ሀሳብ ማቅረብ እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሐምሌ 9 እና 10 የሚካሄደውን የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ንቤንዝያ አክለውም የሩሲያ ቋሚ ልዑክ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት አፈታት ዙርያ ሐምሌ 10 ግልፅ ክርክር ለማካሄድ ፕሮግራም ማስያዙን ጠቁመዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0