የሰኔ 10 የቀትር ዋና ዋና የዓለም ጉዳዮች፡-

ሰብስክራይብ
የሰኔ 10 የቀትር ዋና ዋና የዓለም ጉዳዮች፡- 🟠 በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የሚመራው ኡምኮንቶ ዌ ሲዝዊ ፓርቲ የብሄራዊ አንድነት መንግስትን ምስረታን እንደማይቀላቀል እና ፓርላማ ውስጥ ተቃዋሚዎችን እንደሚመራ ገልጿል። 🟠 በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ልዑክ የወታደሮች መውጣት "የፀጥታ ክፍተት" እንደማይፈጥር ለሀገሪቱ ነዋሪዎች አረጋገጡ። በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልእኮ (አትሚስ) በሶስተኛው ምዕራፍ ወታደራዊ ቅነሳ የባሪሬ ጦር ሰፈርን ለሶማሊያ የጸጥታ ሃይሎች አስረክቧል። 🟠 የሩሲያ የፀጥታ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ በርካታ ሀገራት የብሪክስ ቡድንን ለመቀላቀል እንደሚሹ ገለፁ። 🟠 በሩሲያ ቤልጎሮድ፣ ቮሮኔዝ እና ሊፕትስክ ክልሎች ላይ ስድስት ድሮኖች እንደወደሙ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዘግቧል። 🟠 የኔቶ አባል ሀገራት የሕብረቱን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ወደ ዝግጁነት ደረጃ ለማምጣት ምክክር እያደረጉ እንደሆነ ዋና ፀሐፊው የንስ ስቶልተንበርግ ገለፁ። 🟠 አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወር፣ በስልክ ስርቆት፣ በታጠቁ ጥቃቶች እና በነፍስ ግድያ ጥፋተኛ የተባሉ እስረኞችን ጨምሮ ከ2,750 የሚበልጡ እስረኞች ከዩክሬን እስር ቤቶች ተለቀው በዩክሬን ጦር ኃይሎች ውስጥ እንዲያገለግሉ ተላኩ። 🟠 የምዕራባውያን ሀገራት ንብረቶቿን ለመውረስ ከወሰኑ ሩሲያ መብቷን ለማስጠበቅ "በእጇ ያሉ ሁሉንም መሳሪያዎች" ትጠቀማለች ሲሉ በመንግስታቱ ድርጅት የሩስያ ተወካይ ቫሲሊ ኔቤንዝያ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0