የሮማው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠየቁ

ሰብስክራይብ
የሮማው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠየቁ በሰሜን ኪቩ ግዛት በተፈጠረው ግጭት በአንድ ሳምንት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። ሊቀ ጳጳሱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባደረጉት የእሁድ ጸሎታቸው ከተጎጂዎች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ክርስቲያኖች እንደነበሩ መጥቀሳቸውን የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። "የሀገሪቱ ባለስልጣናት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግጭቱን ለማስቆም እና የዜጎችን ህይወት ለመጠበቅ የተቻላቸውን እንዲያደርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ" ብለዋል። በተጨማሪም የሮማው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን ዩክሬን፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ ሱዳን እና ማይናማርን አንስተው ለሰላም ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰሜን ኪቩ በቅርቡ የተፈፀመው ጥቃት ቢያንስ የ41 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል ሲል የኮንጎ መንግስት ቢገልጽም ከሲቪል ማኅበራት የሚወጡ ዘገባዎች አሃዙን ከፍ አድርገውታል። በክልሉ በዚህ ወር ብቻ 150 ያህል ሰዎችን ለቀጠፈው የደም መፋሰስ መንግሥት ከዳኤሽ ጋር ግኑኝነት አለው የሚባለውን የዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ጥምረት ተጠያቂ አድርጓል። *ዳኤሽ (አይ.ኤስ.አይ.ኤስ/አይ.ኤስ.አይ.ኤል/አይ.ኤስ በመባልም ይታወቃል) በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት ህገወጥ አሸባሪ ድርጅት ነው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0