ታንዛኒያ የአሜሪካ ዶላር አጠቃቀም ላይ ገደብ ጣለች
የታንዛኒያ የፋይናንስ ሚኒስትር ዶ/ር ምዊጉሉ ንቸምባ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የአሜሪካን ዶላር በሀገር ውስጥ ግብይት በስፋት ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚከለክል መመሪያ አውጥተዋል።
2006 በወጣው የታንዛኒያ ባንክ ህግ ክፍል 26 ስር በተደነገገው መሰረት ከሰኔ 24 ጀምሮ ሁሉም ግብይቶች እና ማስታወቂያዎች በታንዛኒያ ሺሊንግ መከናወን አለባቸው።
ዶ/ር ንቸምባ የዶላር አጠቃቀም የዶላር እጥረትና የታንዛኒያ ሺሊንግ ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ አሉታዊ ተፅእኖዎች እንዳሉት ጠቁመዋል። የመንግስት አካላትን ጨምሮ ተቋማት የፋይናንስ መረጋጋትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ለማጎልበት በመመርያው መሰረት
ደንቦቻቸውን እንዲያስተካክሉ ጠይቀዋል።
በተጨማሪም የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። እርምጃው ተቀማጭ የውጭ ምንዛሪን ለመቆጠብ እና የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ለመደገፍ ያለመ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ታንዛኒያ የአሜሪካ ዶላር አጠቃቀም ላይ ገደብ ጣለች
ታንዛኒያ የአሜሪካ ዶላር አጠቃቀም ላይ ገደብ ጣለች
Sputnik አፍሪካ
ታንዛኒያ የአሜሪካ ዶላር አጠቃቀም ላይ ገደብ ጣለች የታንዛኒያ የፋይናንስ ሚኒስትር ዶ/ር ምዊጉሉ ንቸምባ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የአሜሪካን ዶላር በሀገር ውስጥ ግብይት በስፋት ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚከለክል መመሪያ አውጥተዋል። 2006... 16.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-16T14:26+0300
2024-06-16T14:26+0300
2024-06-16T14:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий