በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ሩስያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ ገባ

ሰብስክራይብ
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ሩስያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ ገባ የልዑካን ቡድኑ በብሪክስ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ሩስያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ እንዳቀና ታውቋል። ፎረሙ ከሰኔ 9 እስከ 12 ድረስ ይካሄዳል። በፎረሙ አደም ፋራህን ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ እና የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አዲሱ አረጋ ይሳተፋሉ። ልዑኩ ከፎረሙ ጎን ለጎን የብሪክስ አባል ሀገራት ከሆኑ አቻ የፓርቲ አመራሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያካሄድ ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0