የፑቲን የሰላም ሀሳብ፡ ኔቶ "መተው እንደማይፈልግ እና ወደ ዓለም ጦርነት ሊያመራ የሚችል ጦርነትን መቀጠል እንደሚሻ ግልፅ ነው"

ሰብስክራይብ
የፑቲን የሰላም ሀሳብ፡ ኔቶ "መተው እንደማይፈልግ እና ወደ ዓለም ጦርነት ሊያመራ የሚችል ጦርነትን መቀጠል እንደሚሻ ግልፅ ነው" ፈረንሳዊው ፖለቲከኛ ፍሎሪያን ፊሊፖ የሩስያ ፕሬዝዳንት አርብ ዕለት ያደረጉት ንግግርን በተመለከተ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የለስ ፓትሪዮትስ ፓርቲ መሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት "በምዕራባውያን ሀገሮች፣ በፈረንሳይ እና በሌሎችም አካባቢዎች ያለው የህዝብ አስተያየት የሚስማማ አይደለም። ብዙ ሞት፣ ብዙ ጉዳት፣ በጣም ብዙ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና ድካም አለ።" ፊሊፖት አክለውም “ከግዘ ወደ ግዜ እየሰለቸን ነው፣ ለሰላም መስራታችንን መቀጠል አለብን" ብለዋል። በፖለቲከኛው አስተያየት አሁን ያለው ሁኔታ “የተሳካ የመጀመሪያ የሰላም ሙከራ ከተደረገበት" የመጋቢት 2022ቱ የኢስታንቡል ጉባኤ በጣም ተመሳሳይ ነው። "ሁለቱም አካላት ተቀብለውት የነበረ ቢሆንም ኔቶ ቦሪስ ጆንሰንን በመላክ ዘለንስኪ የሰላም ስምምነቱን እንዳይፈርም በመጨረሻዋ ሰዓት አግዷል።" አሁን ለሩስያ ጥያቄዎች "ጥሩ ግዜ ነው" ያሉት ፖለቲከኛው ጥያቄዎቹ "የተጋነነ እንዳልሆኑ" እና "ተቀባይነት ያላቸው" እንደሆነ ገልፀዋል። እንደ ፈረንሳዊው ፖለቲከኛ ፍሎሪያን ፊሊፖ ገለፃ ኔቶ ግን አዲሱን የሰላም ሃሳብ ወድያው ውድቅ በማድረግ ከ300,000 በላይ ሰራዊት ሊያንቀሳቅስ እንደሚችል አስታወቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0