የፈረንሳዩ ኦራኖ ኒጀር በሚገኘው ኢሞራረን ማዕድን ማውጫ ስፍራ ዩራኒየም የማምረት መብቱን ሊያጣ እንደሚችል ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
እንደ ዘገባው ከሆነ የፈረንሳዩ ኩባንያ ከኒጀር ባለስልጣናት ጋር የውል ማራዘሚያ ስምምት ላይ መድረስ አልቻለም።
ኦራኖ የተሰኘው የማዕድን ኩባንያ በዓለም ከፍተኛ ክምችት በሚገኝበት የማዕድን ቦታ ዩራኒየም ማውጣት የሚያስችለውን መብት ከሰኔ 12 ጀምሮ ሊያጣ እንደሚችል ተገልጿል።
በዜና ወኪሉ የታየ የኒጀር ማዕድን ሚኒስቴር ደብዳቤ የማዕድን ስፍራውን ክምችት ለማዳበር የቀረበው ዕቅድ "የመንግሥትን ፍላጎት አላሟላም" ማለቱን አመላክቷል። የኒጀር ባለስልጣናት "ሁለተኛው እና የመጨረሻው ማስታወቂያ ሰኔ 12 እንደሚያበቃ እና ከዚያ ቀን በኋላ የኩባንያው የስራ ፍቃድ እንደሚሰረዝ" አስታውቀዋል።
ኢሞራረን 200,000 ቶን የሚገመት ክምችት በመያዝ በዓለም ከፍተኛ የዩራኒየም ክምችት ከሚገኝባቸው ቦታዎች አንዱ ነው።
ኦራኖ ኢሞራረን ውስጥ አብላጫውን ድርሻ ሲይዝ የኒጀር ሶፓሚን ቀሪውን 33.35% ይቆጣጠራል።
ኦራኖ በ2021 ኮሚናክ የማዕድን ስፍራ መዘጋቱን ተከትሎ በሰሜን አርሊት ክልል በሚገኘውን ሶሜር ክፍት ጉድጓድ እየሰራ ይገኛል። በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር መፈንቅለ መንግሥት መካሄዱን ተከትሎ ከተፈጠረ የበርካታ ወራት የምርት መቋራረጥ በኋላ የሶሜር የማዕድን ስፍራ በየካቲት ወር ነበር በድጋሚ ስራ የጀመረው።
ኢሞራረን የማዕድን ማውጫ ቦታ የሚካሄዱ ስራዎች ከ2015 ጀምሮ እንደተቋረጡ የኩባንያው ድረ-ገጽ አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የፈረንሳዩ ኦራኖ ኒጀር በሚገኘው ኢሞራረን ማዕድን ማውጫ ስፍራ ዩራኒየም የማምረት መብቱን ሊያጣ እንደሚችል ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
የፈረንሳዩ ኦራኖ ኒጀር በሚገኘው ኢሞራረን ማዕድን ማውጫ ስፍራ ዩራኒየም የማምረት መብቱን ሊያጣ እንደሚችል ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
Sputnik አፍሪካ
የፈረንሳዩ ኦራኖ ኒጀር በሚገኘው ኢሞራረን ማዕድን ማውጫ ስፍራ ዩራኒየም የማምረት መብቱን ሊያጣ እንደሚችል ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ እንደ ዘገባው ከሆነ የፈረንሳዩ ኩባንያ ከኒጀር ባለስልጣናት ጋር የውል ማራዘሚያ ስምምት ላይ መድረስ... 15.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-15T19:59+0300
2024-06-15T19:59+0300
2024-06-15T20:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የፈረንሳዩ ኦራኖ ኒጀር በሚገኘው ኢሞራረን ማዕድን ማውጫ ስፍራ ዩራኒየም የማምረት መብቱን ሊያጣ እንደሚችል ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
19:59 15.06.2024 (የተሻሻለ: 20:20 15.06.2024)
ሰብስክራይብ