ጋምቢያ በትምህርት ዘርፍ የሩስያን እውቀት እንደምትሻ እና ለጋምቢያ ተማሪዎች የትምህርት እድል ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች
ሩስያ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ለጋምቢያ ተማሪዎች የምትሰጠውን የነፃ ትምህርት ዕድል ከ12 ወደ 50 እንደምታሳድግ ቃል መግባቷን ካዛን ሩስያ ሰኔ 3 እና 4 ተካሂዶ ከነበረው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የትምህርት ሚኒስትሮች መድረክ ጎን ለጎን ቃለ መጠይቅ የሰጡ የጋምቢያ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
"ሀገራዊ የልማት ግቦቻችንን እውን ማድረግ የምንችለው በትምህርት ብቻ ነው" ሲሉ በሩስያ የጋምቢያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ኢብራሂም ሲሳይ አፅንዖት ሰጥተዋል። "የጋምቢያ ተማሪዎች ወደ ሩስያ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይማራሉ ይህ የጋምቢያን የነፃ ትምህርት መደብ ይጨምራል።"
የመሠረታዊና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሚኒስትር ሃዲ ጃቱ ሴይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞችን አስፈላጊነት ገልፀው የጋምቢያ መንግሥት ወጣቶችን አስፈላጊ ክህሎት በማስያዝ ለሠራተኛው ኃይል አስተዋፅኦ የሚያደርጉበትን መንገድ እየፈለገ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማሳደግ የቅድመ-አገልግሎት እና የአገልግሎት ላይ የአስተማሪዎች ስልጠናን በተመለከተ የሩስያን ድጋፍ እንደሚሹ አስታውቀዋል።
"ወጣቶች ለሠራተኛው ሃይል የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ የቴክኒክ ክህሎት እና እውቀት የሚያገኙበት አማራጭ ስርዓት ማግኘት አለብን፤ ሩስያ በጣም ጠንካራ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች እንዳሏት እናውቃለን" ብለዋል ሚኒስትር ሴይ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ጋምቢያ በትምህርት ዘርፍ የሩስያን እውቀት እንደምትሻ እና ለጋምቢያ ተማሪዎች የትምህርት እድል ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች
ጋምቢያ በትምህርት ዘርፍ የሩስያን እውቀት እንደምትሻ እና ለጋምቢያ ተማሪዎች የትምህርት እድል ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች
Sputnik አፍሪካ
ጋምቢያ በትምህርት ዘርፍ የሩስያን እውቀት እንደምትሻ እና ለጋምቢያ ተማሪዎች የትምህርት እድል ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች ሩስያ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ለጋምቢያ ተማሪዎች የምትሰጠውን የነፃ ትምህርት ዕድል ከ12 ወደ 50 እንደምታሳድግ ቃል... 15.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-15T16:33+0300
2024-06-15T16:33+0300
2024-06-15T17:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ጋምቢያ በትምህርት ዘርፍ የሩስያን እውቀት እንደምትሻ እና ለጋምቢያ ተማሪዎች የትምህርት እድል ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች
16:33 15.06.2024 (የተሻሻለ: 17:20 15.06.2024)
ሰብስክራይብ