የአፍሪካ ሀገራት በዩክሬን ግጭት ዙርያ ስለሚካሄደው የስዊዘርላንድ የሰላም ኮንፈረንስ ምን ያስባሉ?

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት በዩክሬን ግጭት ዙርያ ስለሚካሄደው የስዊዘርላንድ የሰላም ኮንፈረንስ ምን ያስባሉ? ኮንፈረንሱ ሰኔ 8-9 በስዊዘርላንዷ ከተማ ሉሰርን ይካሄዳል። ሩስያ በዝግጅቱ ላይ አትሳተፍም። የደቡብ አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ከሩስያ ውጪ የሚደረግ ስብሰባ በቂ እንዳልሆነ ገልፀው የሰላም ውይይት አይደለም፣ “አውደ ጥናት ነው” ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። "የሩስያን የሰላም እቅድ ማየት እንፈልጋለን። ሁለቱን አንድ ላይ ማሰባሰብና የሚያቀርቡትን ዕቅድ ማየት አለብን" ሲሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ናሌዲ ፓንዶር አክለዋል። የኮንጎ ብራዛቪል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን ክላውድ ጋኮሶ "ሩስያን የማያሳተፍ የትኛውም ድርድር ትርጉም የለሽ እንደሆነ አምነዋል" ሲሉ የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ባለፈው ሳምንት ከጋኮሶ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ጋኮሶ በበኩላቸው "ሩስያ ለምን ከዚህ ጉባኤ እንደተገለለች አልገባንም፤ ይህ የሰላም ኮንፈረንስ ነው ወይ የሚል ጥያቄ ጭሮብናል" ብለዋል። ያለ ሩስያ ተሳትፎ በዩክሬን ዙርያ የሰላም ኮንፈረንስ ማካሄድ ስህተት ነው ሲሉ የቻድ የኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር አብድራማን ኩላማላህ ባለፈው ሳምንት ከላቭሮቭ ጋር በጋራ በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኮንፈረንሱ በሞስኮ ላይ ቅድመ ሁኔታዎችን ለመጫን የሚደረግ ጥረት እንደሆነ እና ሩስያ ላይ ስትራቴጂካዊ ሽንፈት ለማድረስ እንደተረገው ሙከራ አይሳካም ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0