በተመድ የሩስያ ልዑክ የፀጥታው ምክር ቤት ሱዳን ላይ ያቀረበውን ረቂቅ ምክረ ሀሳብ ከእውነታ የራቀ እና የሱዳናውያንን "መርህ ተኮር አስተያየቶች" ችላ ያለ ብሎታል

ሰብስክራይብ
በተመድ የሩስያ ልዑክ የፀጥታው ምክር ቤት ሱዳን ላይ ያቀረበውን ረቂቅ ምክረ ሀሳብ ከእውነታ የራቀ እና የሱዳናውያንን "መርህ ተኮር አስተያየቶች" ችላ ያለ ብሎታል በተባበሩት መንግሥታት የሩስያ ምክትል ቋሚ ተወካይ አና ኢቪስቲግኒቫ በረቂቅ ሰነዱ ድምፅ አሰጣጥ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንደማይቻል ተናግረዋል። በፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት "የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በሱዳን ያለውን ውስብስብ ሁኔታ ለመፍታት የሚያስችል ምንም አይነት ተጨባጭ ሀሳቦችን አልያዘም። ሰነዱ የሱዳንን አስተያየት ግንዛቤ ውስጥ ያልከተተ እና በተደረሱ ስምምነቶች ላይ የተመሰረተ አይደለም" ሲሉ አብራርተዋል። ሐሙስ እለት የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት በዩናይትድ ኪንግደም የቀረበውን እና ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ በምዕራብ ሱዳን በምትገኘው የአል ፋሸር ከተማ እያካሄደ ያለውን ከበባ እንዲያቆም እና በከተማው ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ የሚያቀርበውን ምክረ ሀሳብ ተቀብሏል። የውሳኔ ሃሳቡን 14 ሀገራት ሲደግፉት ሩስያ ድምፅ ከመስጠት ተቆጥባለች። ኢቪስቲግኒቫ ሩስያ የፀጥታው ምክር ቤት "አባል ሀገራት" የሱዳንን ሰብዓዊ ተደራሽነት ለማረጋገጥ ከመልካም ዓላማዎች ጀርባ መደበቅ እንዲያቆሙ ትጠይቃለች ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0