ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል "በህገ-ወጥ መንገድ የተዘረፈ" ማዕድናትን በመጠቀሙ ሳቢያ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እያሰበ ነው።

ሰብስክራይብ
ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል  "በህገ-ወጥ መንገድ የተዘረፈ" ማዕድናትን በመጠቀሙ ሳቢያ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እያሰበ ነው። በሚያዝያ ወር፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን የሚወክሉ ጠበቆች በፓሪስ አፕል ኩባንያን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወደ ሩዋንዳ በህገ ወጥ መንገድ የተጓጓዙ ማዕድናትን "በአለምአቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት" ውስጥ እንዲገባ አድርጓል በሚል ክስ ማቅረባቸው ይታወሳል። ጠበቃ ዊልያም ቦርደን ሐሙስ ዕለት በሰጠው አስተያየት አፕል ለቀረበበት ክስ  አጭር ምላሽ መስጠቱን ተናግሯል፤ መልሱ “ንቀትን ፣ እና እብሪተኝነትን ያሳያል” በማለት ተናግሯል ። የመንግስት የህግ ቡድን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ተሰብስቦ ጉዳዩን በሚመለከት ያሉ ስልታዊ አማራጮች ዙሪያ  ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኪዲ ጋር ተወያይቷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0