የሰኔ 7 ረፋድ ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሰኔ 7 ረፋድ ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ ሃይሎች 70 የዩክሬን ድሮኖች በሀገሪቱ የሮስቶቭ ክልል ግዛት ፤እንዲሁም  17 የሚደርሱትን ደግሞ በሩሲያ ቤልጎሮድ፣ ቮልጎግራድ፣ ቮሮኔዝ እና ኩርስክ ክልሎች እና ክራይሚያ ግዛቶች ላይ ማውደሙንየሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል። 🟠 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች  በሩሲያ ቮሮኔዝ ክልል የሚገኘውን የነዳጅ ማከማቻ መጋዘን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት፣ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ታንከሮች ላይ ጎዳት ሲደርስ በሰው ላይ ግን ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን  የክልሉ ገዥ ተናግረዋል ። 🟠  ዩክሬን ኔቶን እንድትቀላቀል ለመርዳት የተነደፈውን የደህንነት ዋስትና ስምምነት አሜሪካ እና ዩክሬን መፈራረማቸውን የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 ኔቶ በዩክሬን ያለው ተልዕኮ አካል የሆነና በፖላንድ፣ በሮማኒያ እና በስሎቫኪያ የጦር መሳሪያ አቅርቦቶችን ለኪዬቭ የሚያስተባብር የጦር ሰፈሮችን ማቋቋም እንደሚያስፈልግ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ገለፁ። 🟠 የአሜሪካው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተግባብተው ሊሰሩ የሚችሉበትንምክንያትሲያስረዱ፤ ከጠንካሮች ጋር መሥራት ስለሚሻል ነው ብለዋል። ትራምፕ የዩክሬንን ቀውስ ለመፍታት ከሩሲያ የዩኤፍሲ ተዋጊ ካቢብ ኑርማጎሜዶቭ ጋር መወያየታቸውን እና በአሜሪካ ምርጫ እርሳቸው ካሸነፉ ፤ ግጭቱን ወዲያውኑ እንደሚያስቆሙ ቃል ገብተውላቸዋል። 🟠 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በልጃቸው ሀንተር ላይ ፍርድ ቤቱ የሚያስተላልፈውን ውሳኔ እንደሚቀበሉ እና እርሳቸውም ይቅርታ እንዳማያደርጉላቸው  ተናግረዋል ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0