በውስብሰብ እና ተደራራቢ ጦርነቶች ሳቢያ በአለም አቀፍ ደረጃ በግጭት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ30 በመቶ ማደጉን አንድ ጥናት አመላከተ።

ሰብስክራይብ
በውስብሰብ እና ተደራራቢ ጦርነቶች ሳቢያ በአለም አቀፍ ደረጃ በግጭት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ30 በመቶ ማደጉን አንድ ጥናት አመላከተ። ከኦስሎ ሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት (PRIO) የወጣው አዲስ ጥናት እንዳለው ከሆነ በዓለምአቀፍ ደረጃ በግጭት ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን አመላክቷል። እ.ኤ.አ በ2024 በጦር ሜዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ካለፉት ሁለት ዓመታት አንፃር በትንሹ ቢቀንስም፣ ከ2021 ጀምሮ አጠቃላይ ከግጭት ጋር የተያያዙ የሟቾች ቁጥር ፤ንፁሃን ዜጎችን ጨምሮ በአሳሳቢ ደረጃ ከፍ ብሏል። ሪፖርቱ  በአስደንጋጭ ሁኔታ ለጨመረው የሞት ቁጥር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የነበረውን የእርስ በርስ ጦርነትን፣ የሩስያ እና የዩክሬን ግጭትን፣ የእስራኤል የጋዛ የቦምብ ጥቃትን እና በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ግጭት በዋናነት ጠቅሷል። በትግራይ የነበረው ግጭት ባለፈው አመት በተኩስ አቁም ስምምነት ቢቆምም ፤ እ.ኤ.አ  በ 2023 አሁንም ከግጭት ጋር በተያያዘ 122,000 ሰዎች በግጭት ሳቢያ ሞተዋል፤ በዩክሬን        ከ 71,000 በላይ ፤በጋዛ ደግሞ 23,000 የሚደርሱ ሰዎች መሞታቸውን ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ በ34 ሀገራት እንዲሁም በ59 የግጭት ቀጠናዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፤የዓለማችን የግጭት ገጽታ ውስብስብነት እየጨመረ መምጣቱን አመልክቷል። በድርጅቱ የምርምር ፕሮፌሰር የሆኑት ሲሪ አስ ሩስታድ እንዳሉት “በአለም ላይ የሚካሄዱ ግጭቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ” ብለዋል። የግጭቶች ውስብስብነት እየተባባሰ መምጣቱን፣ በግጭት ከተጎዱት ሀገራት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በርካታ ግጭቶች ሲያስተናገዱ ፤ሰባት ሀገራት ደግሞ በአንድ ጊዜ ከሶስት በላይ ግጭቶችን እንዳስተናዱ ፕሮፌሰሯ ጠቁመዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0