በአፍሪካ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን መዋጋት፡ ሚዛናዊ አቀራረብን የሚፈልግ ዘርፈ ብዙ ፈተና እንደሆነ ተገለፀ።

ሰብስክራይብ
በአፍሪካ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን መዋጋት፡ ሚዛናዊ አቀራረብን የሚፈልግ ዘርፈ ብዙ ፈተና እንደሆነ ተገለፀ። በአፍሪካ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ መስፋፋት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው፤ይህንንም ችግር ለመዋጋት ሁሉን አቀፍ አካሄድ እንደሚያስፈልግ በአፍሪካ ህጻናት ፖሊሲ መድረክ የህፃናት እና የህግ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ኢዛቤል ማጋያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ሰኔ 12 ቀን የሚከበረው የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ ቀንን አስመልክቶ ተናግረዋል። ማጋያ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት "ከፍተኛ የድህነት ደረጃ ትልቁ ምክንያት ነው። "ልጆች የአዋቂዎች እንክብካቤ ሲያጡ ራሳቸውን ለማሸነፍ ለጉልበት ብዝበዛ የሚዳርግ የሥራ መሥክ ላይ ይሰማራሉ" ከድህነት ውጪ ግጭት እና የአየር ንብረት ለውጥ ህጻናትን ለጉልበት ብዝበዛ የሚዳርጉ ምክንያቶች ሲሆኑ ፤ ህፃናቱም በግብርና፣ በአሳ ማጥመድ፣ በማእድን እና በግንባታ እና ሌሎች ዘርፎች ውስጥ እንደሚሰማሩ የህጻናት መብት ተሟጋቿ ተናግሯል። ባርነትንና ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ጨምሮ አስከፊው የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ በአንዳንድ የአፍሪካ አካባቢዎች ይበልጥ መስፋፋቱን ተናግራለች። ምንም እንኳን የወጡ ህጎች ቢኖሩም ፣ ባለማወቅ ፣በሙስና እንዲሁም በቂ የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ሳቢያ አፈፃፀሙ አሁንም አስቸጋሪ ነው። "ጎጂ የሆኑ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን ከጠቃሚው መለየት አለብን። ህፃናት ከእድሜ ጋር የሚስማማ ስራ እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል" ሲሉ ማጋያ ተናግረዋል ።"ሕጻናት ያላቸው መብቶች በወረቀት ላይ የተቀመጡ መብቶች ብቻ ሳይሆኑ በተግባር የሚተረጎሙ ህይወታቸውን የሚለውጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብን። በመጨረሻም  በአፍሪካ የሕፃናት ላይ የሚፈፀመው የጉልበት ብዝበዛ ለአፍሪካ አህጉር እንቅፋት መሆኑን መናገር እፈልጋለሁ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0