በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአለም ላይ እጅግ የከፋ ነው ብሎ በገለጸው የሱዳን ስደተኞች ሁኔታ፤ ግጭቱ ከጀመረበት እ.አ.አ ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ 7.26 ሚሊዮን አዲስ ተፈናቃዮች እና 2.83 ሚሊዮን ከዚህ ቀደም የተፈናቀሉ ዜጎች መኖራቸው አስታወቋል።
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አክሎም ከ2 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን አስታውቋል።
በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ፤በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ሲገለፁ ምናልባትም ቁጥሩ እስከ 150,000 ሊደርስ እንደሚችል ግምት አለ።እንዲሁም ዜጎች በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ እና በተለይ በዋና ከተማዋ ካርቱም የከፋ ውድመት እየደረሰ መሆኑ ተነግሯል።
ይህ በጦርነት ምክንያት የተፈናቀለው ዜና በሱዳን ከፍተኛ የሆነ ረሃብ ያስከተለ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጦት የደረሰ እና የእርዳታ አቅርቦት ላይ እክል የፈጠረ በመሆኑ፤ አስከፊ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ ፈጥሯል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ አቅርቦትን የሚያደናቅፉ "ስልታዊ እንቅፋቶች" መኖሩን አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
Sputnik አፍሪካ
በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአለም ላይ እጅግ የከፋ ነው ብሎ በገለጸው የሱዳን ስደተኞች ሁኔታ፤ ግጭቱ ከጀመረበት እ.አ.አ... 12.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-12T19:40+0300
2024-06-12T19:40+0300
2024-06-12T20:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
19:40 12.06.2024 (የተሻሻለ: 20:20 12.06.2024)
ሰብስክራይብ