ሩሲያ እና ሱዳን በቀይ ባህር ዳርቻ የባህር ሃይል ጦር ሰፈር ለመገንባት እስካሁን ስምምነት ላይ እንዳልደረሱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ።

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ሱዳን በቀይ ባህር ዳርቻ የባህር ሃይል ጦር ሰፈር ለመገንባት እስካሁን ስምምነት ላይ እንዳልደረሱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ። "በጉዳይ ላይ እየተወያየን ነው፤ እኔ እስከማውቀው ድረስ የተደረሰ ምንም ዓይነት ሥምምነት የለም፤ በወታደራዊ ዲፓርትመንቶች በኩልም የተደረሰ ስምምነት የለም።" ሲሉ ሚካሂል ቦግዳኖቭ ማክሰኞ እለት ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ማሊክ አጋር፤ በሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት ፤ሱዳን በቀይ ባህር ላይ ከሩሲያ ጋር የባህር ኃይል ጦር ሰፈር ለመገንባት በተደረሰው ስምምነት እንዲፈፀም ትፈልጋለች ብለዋል። የሌሎች ሀገራትን አስተያየት ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚያስፈልግም አክለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0