የማላዊው ፕሬዝዳንት በአውሮፕላን አደጋ ለሞቱት ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሎስ ክላውስ ቺሊማ እና ሌሎች ስምንት ባለስልጣናት የ3 ሳምንት ሀዘን አወጁ።
የማላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ላዛሩስ ማካርቲ ቻክዌራ ሀገሪቱ እ.አ.አ ከሰኔ 11 ቀን 2024 እስከ ሰኞ ሰኔ 1 ቀን 2024 ድረስ የሚቆይ የሐዘን ቀናት ማወጃቸው ተነግሯል። የማላዊ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሎስ ክላውስ ቺሊማ እና ሌሎች ባለሥልጣናት ፤ ሰኞ ሰኔ 10 ቀን 2024 በቺካንጋዋ ማዚምባ አቅራቢያ በደረሰ አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ መሞታቸውን የሀገሪቱ መንግስት በሰጠው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።
ቻኩዌራ በታወጀው ብሔራዊ ሀዘን ቀናት ሁሉም ባንዲራዎች ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡ መመሪያ ሰጥተዋል።
የአደጋው ተጎጂዎች አስከሬን ወደ ሀገሪቱ ዋና ከተማ ሊሎንግዌ መጓጓዙን የማላዊው ፕሬዝዳንት በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው የሀዘን መግለጫ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም ለማላዊ መንግስት እና ህዝብ መጽናናትን ተመኝቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የማላዊው ፕሬዝዳንት በአውሮፕላን አደጋ ለሞቱት ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሎስ ክላውስ ቺሊማ እና ሌሎች ስምንት ባለስልጣናት የ3 ሳምንት ሀዘን አወጁ።
የማላዊው ፕሬዝዳንት በአውሮፕላን አደጋ ለሞቱት ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሎስ ክላውስ ቺሊማ እና ሌሎች ስምንት ባለስልጣናት የ3 ሳምንት ሀዘን አወጁ።
Sputnik አፍሪካ
የማላዊው ፕሬዝዳንት በአውሮፕላን አደጋ ለሞቱት ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሎስ ክላውስ ቺሊማ እና ሌሎች ስምንት ባለስልጣናት የ3 ሳምንት ሀዘን አወጁ። የማላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ላዛሩስ ማካርቲ ቻክዌራ ሀገሪቱ እ.አ.አ ከሰኔ 11 ቀን 2024 እስከ... 12.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-12T18:07+0300
2024-06-12T18:07+0300
2024-06-12T18:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የማላዊው ፕሬዝዳንት በአውሮፕላን አደጋ ለሞቱት ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሎስ ክላውስ ቺሊማ እና ሌሎች ስምንት ባለስልጣናት የ3 ሳምንት ሀዘን አወጁ።
18:07 12.06.2024 (የተሻሻለ: 18:40 12.06.2024)
ሰብስክራይብ