ፑቲን በአለም አቀፍ ሳይንሳዊ የጨረቃ ጣቢያ ግንባታ ላይ ከቻይና ጋር ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ፈረሙ።

ሰብስክራይብ
ፑቲን በአለም አቀፍ ሳይንሳዊ የጨረቃ ጣቢያ ግንባታ ላይ ከቻይና ጋር ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ፈረሙ። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአለም አቀፍ ሳይንሳዊ የጨረቃ ጣቢያን በጋራ ለመማቋቋም  ከቻይና ጋር የተደረገውን ስምምነት የሚያፀድቀውን ህግ መፈረማቸውን ፤ በዛሬው እለት በይፋዊው የሕግ መረጃ ፖርታል ላይ የወጣው ሰነድ አመላክቷል። በመጋቢት ወር ላይ የሩሲያ መንግስት ከቻይና ጋር የተደረሰውን ስምምነት የሚያፀድቅበትን ረቂቅ ለፓርላማው አቅርቦ ነበር። በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ የሩሲያ የጠፈር ኮርፖሬሽን ሮስኮስሞስ ኃላፊ ዩሪ ቦሪሶቭ ለስፑትኒክ እንዳረጋገጡት እ.ኤ.አ ከ2033-2035 ሩሲያ የኒክሌር ኃይል ማመንጫ ልማትን ከቻይና ጋር በጋራ ወደ ጨረቃ ለመላክ ቀደም ብለው የቀዱት እቅድ መጀመሩን አረጋግጠዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0