የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ስለፈፀሙት ዮዲት ሱሚንዋ ቱሉካ ምን ይታወቃል?

ሰብስክራይብ
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ስለፈፀሙት ዮዲት ሱሚንዋ ቱሉካ ምን ይታወቃል? ▪ ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት የሆኑት የ56 ዓመቷ ሴት የተወለዱት በሀገሪቱ ኮንጎ ሴንትራል ግዛት ነው። ▪ ከብራሰልሱ ፍሪ ዩኒቨርሲቲ በሠራተኛ አስተዳደር ሳይንስ እና በሰው ሀብት አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ ይዘዋል። ▪ በቤልጂየም ከሚገኘው የሞንስ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲዎች በአፕሊድ ኢኮኖሚክስ፣ ኦፕሽን ፋይናንሺያል ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። ▪ አዲስ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ብራስልስ ከሚገኘው የፕሮሞሽንና ተከታታይ ትምህርት ክፍል በአካውንቲንግ ዲግሪ አግኝተዋል። ▪ መጀመሪያ የሥራ ዓለም በባንክ ዘርፍ የሰሩ ሲሆን ወደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት፤ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ቢሮ ጭምር ሠርተዋል። ▪ እ.ኤ.አ በ2012 ቱሉካ ሱሚንዋ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የበጀት ሚኒስትር አማካሪ ሆነው ሰርተዋል። ▪ በመቀጠልም በሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት የስትራቴጂክ ክትትል ምክትል አስተባባሪ በመሆን አገልግለዋል። ▪ እ.አ.አ ከመጋቢት 24 ቀን 2023 ጀምሮ ቱሉካ ሱሚንዋ የUገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማት ፖሊሲ በማቀድ እና ፕሮግራም በማዘጋጀት የሀገሪቱን የፕላን ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0