ቱርክ የብሪክስ ህብረትን ለመቀላቀል ያላትን ፍላጎት ሩሲያ በደስታ እንደምትቀበለው ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ።

ሰብስክራይብ
ቱርክ የብሪክስ ህብረትን ለመቀላቀል  ያላትን ፍላጎት ሩሲያ በደስታ እንደምትቀበለው ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ። "ቱርክ ብሪክስ ለመቀላቀል  ያላትን ፍላጎት በደስታ እንቀበላለን፤ይህንን ፍላጎት  በሁሉም ረገድ እንደግፋለን፤ እናም የጋራ ችግሮችን ለመፍታት ከህብረቱ አባል ሀገራት ጋር በጋራ እንሰራለን" ሲሉ ከቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ጋር በነበራቸው ውይይት ገልፀዋል። በተጨማሪም ሩሲያ ከቱርክ ጋር ባላት ግንኙነት ደስተኛ ነች ሲሉ ፕሬዚዳንቱ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። "ከቱርክ ጋር ባለን ግንኙነት ደስተኞች ነን። ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን አመራር እና ቀጥተኛ ድጋፍ ነው" ብለዋል ፑቲን። ቭላድሚር ፑቲን በሚቀጥለው ወር ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በአስታና የመገናኘት እቅድ እንዳላቸው ጠቅሰዋል። " ለፕሬዚዳንት ኤርዶጋን መልካም ምኞቴን እንዲያደርሱልኝ  እጠይቃለሁ ።   እስከማውቀው ድረስን  በሐምሌ ወር (ከሐምሌ 3-4 ) በአስታና በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንገናኛለን የሚል ተስፋ አለኝ። በዚህ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተገናኝተን ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች የመወያየት እድል ይኖረናል ብዬ አምናለሁ። " ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል። ሃካን ፊዳን ከፑቲን ጋር ከመገናኘቱ በፊት የብሪክስ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባን በሩሲያዋ ኒዝሂ ኖቭጎሮድ ከተማ ታድመዋል። ከስብሰባው ጎን ለጎን በተለይ ከኢትዮጵያ አቻቸው አምባሳደር ታዬ አጽቅስላሴ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0