በሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም#SPIEF2024 73 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ከ1,000 በላይ ስምምነቶችን መፈረማቸውን አዘጋጆቹ ተናገሩ።

ሰብስክራይብ
በሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም#SPIEF2024 73 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ከ1,000 በላይ ስምምነቶችን መፈረማቸውን አዘጋጆቹ ተናገሩ። "ፎረሙ 1,073 ስምምነቶችን በድምሩ 6.492 ትሪሊየን ሩብል( ሚስጥራዊ የሆኑ ስምምነቶችን ሳይጨምር) እንዲሁም  ከውጭ ኩባንያዎች ተወካዮች ጋር የተፈረሙ 55 ስምምነቶች  እንደጨምር"  ዝግጅቱን ያዘጋጀው የሩሲያው ሮስኮንግሬስ ፋውንዴሽን በመግለጫው አስታውቋል። በሩሲያ መንግስት ኮርፖሬሽን ቬብ አር ኤፍ (VEB.RF ) እና በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኩባንያ ሩስ ሃይድሮ (RusHydro) መካከል የተደረገው ስምምነት ፤ በዋጋ ሆነ በአስፈላጊነቱ  ትልቅ ትርጉም ያለው ሲሆን ከዋጋ አንፃር 650 ቢሊዮን ሩብል የሚገመት እንደሆነ ፋውንዴሽኑ ተናግሯል። 1.3 ትሪሊዮን ሩብል ዋጋ ያላቸውን 69 ስምምነቶች በመፈረም የሩስያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ቀዳሚ ስትሆን፤ በአጠቃላይ 251የሚሆኑ ስምምነቶች በሩሲያ ግዛቶች መካከል በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት መስክ የተፈረሙ ስምምነቶች ናቸው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0