ሩሲያ እና ጅቡቲ በትምህርትና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማስፋት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እየተወያዩ ነው ።

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ጅቡቲ በትምህርትና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማስፋት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እየተወያዩ ነው ። “ጅቡቲ በፍጥነት  እያደገች ያለች ሀገር ነች። ዛሬ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ አላት። እያንዳንዱ አገር የሚለይበት ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነኝ ፤ስለዚህ ልምድ እና ምርጥ ተሞክሮዎችን መለዋወጥ ለእኛ አስፈላጊ ነው። የትምህርት ደረጃዎቻችንን ልኬታችንን ፣ የትምህርት ተቋሞቻችንን መሠረተ ልማት ለማሳየት እና መምህራኖቻችን በአሁኑ ጊዜ ተማሪዎችን በሚያስተምሩባቸው ፕሮግራሞች ላይ ግንዛቤዎችን ለመስጠት ዝግጁ ነን ብለዋል የሩሲያ የትምህርት ሚኒስትር ሰርጌ ክራቭትሶቭ። የጅቡቲ አቻው ሙስጠፋ መሀመድ መሃሙድ በበኩላቸው፤ ከሩሲያ የትምህርት ሚኒስቴር ጋር ያለውን ትብብር ለማስፋት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል ። አገራቸው በሁሉም መስኮች እያደገች መሆኗን ጠቅሰዋል፤ ስለዚህም ከሀገሪቱ ዋና ተግባራት አንዱ በየዘርፉ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት እንደሆነ ተናግረዋል ነው። አፍሪካዊቷ ሀገር በዲጂታል ቴክኖሎጂ መስክ ልዩ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ከሩሲያን ልምድ መቅሰም እንደሚፈልግም ጠቁመዋል። ስብሰባው የተካሄደው በሩሲያ ካዛን ከተማ እ.አ.አ ሰኔ 10-11 በተካሄደው በሁለተኛው ዓለም አቀፍ የትምህርት ሚኒስትሮች መድረክ ዋዜማ ላይ ነው ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0