የሰኔ 4 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሰኔ 4 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 የማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንትን እና አጃቢዎቻቸውን አሳፍሮ የነበረው አይሮፕላን ተከስክሶ አንድም ሰው አለመትረፉ ተዘግቧል።የነፍስ አድን ሰራተኞች በዛሬው እለት የተከሰከሰውን አውሮፕላን ቁርጥራጭ አግኝተዋል። 🟠 የአሜሪካ  አስተዳደር ለዩክሬን ብሄራዊ ሻለቃ "አዞቭ" (በአሸባሪ የተፈረጀና በሩሲያ ታግዶ የነበረ ድርጅት) የጦር መሳሪያ አቅርቦት እገዳ እንደ ተነሳለት፤ የስቴት ዲፓርትመንትን ጠቅሶ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። 🟠 ስትራቴጂካዊ ያልሆኑ የኒውክሌር ማሳሪያ ልምምድ ሁለተኛው ምዕራፍ መጀመሩን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዘግቧል። 🟠 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቀደም ሲል በባይደን የቀረበው የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እቅድ ማፅደቁ ተገለፀ 🟠 ዳኞች የባይደን ልጅ የጦር መሳሪያ መያዝን በሚመለከት ብይን መስጠት አልቻሉም። ብይን ለመስጠት ለዛሬ መቀጠሩን የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 አሜሪካዊው ስራ ፈጣሪ ኢሎን መስክ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎች በስርዓተ ክወና ደረጃ ከተቀናጁ የአፕል ምርቶችን በድርጅቶቻቸው ውስጥ መጠቀምን ሊያግዱ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0